ኢትዮጵያ የወረቀት ገንዘቦቿን ለውጥ አደረገች፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለ 200 ብር ኖቶችም ታትመዋል

ኢትዮጵያ የወረቀት ገንዘቦቿን ለውጥ አደረገች፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለ 200 ብር ኖቶችም ታትመዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ በገበያ ላይ ባሉት የወረቀት ገንዘቦቿ ላይ ለውጥ አደረገች፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረቀት ገንዘቧ ውስጥ ባለ 200 ብር ኖቶችን መጠቀም መጀመሯን ይፋ አድርጋለች።

ሃገሪቱ ከዛሬ ጀምሮ አገሪቱ የ10፣ 50 እና 100 ብር ኖቶቿን ከመቀየሯ ባሻገር፤ ቀደም ሲል ያልነበረው የ200 ብር ኖትን በሥራ ላይ አውላለች።
 አዲሶቹን የገንዘብ ኖቶች ይፋ ማድረግ ያስፈለገው ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ታስቦ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ከዚህ በተጨማሪ አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲኖራቸው የተደረጉት የደኅንነት ገጽታዎች አመሳስሎ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችን ለማስቀረት እገዛው የጎላ ነው ብለዋል።
መንግሥት ለብር ለውጡ ከላይ የተቀመጡትን ነጥቦች በምክንያትነት ቢዘረዝርም ቀደም ሲል በቢሊየን የሚቆጠሩ ጥሬ ገንዘቦች ከባንክ ውጭ በግለሰቦች እጅ ይገኛሉ ሲል መግለፁን ተከትሎ እነዚህን የተበታተኑ ገንዘቦች ለመሰብሰብ ታስቦ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል።

LEAVE A REPLY