ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ዛሬ የለወጠችው አዲስ የብር ኖትን ለመቀየር ከ 3 ወር በላይ ጊዜ መፍጀት እንደማይችል የብሔራዊ ባንክ እወቁልኝ ሲል ገለጸ።
የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ፤ ከ100 ሺኅ ብር በላይ ያላቸው ሰዎች በ1 ወር ወስጥ ገንዘባቸውን ሊቀይሩ እንደሚችሉም አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ አሮጌ ብሯን ለውጣ ለመጨረስ ከ 2 እስከ 3 ወር የጊዜ ገደብ ያስቀመጠች ሲሆን፣ ከተቻለ በ 2 ወር ካልተቻለም በ 2 ወር ተኩል የተለየ ጉዳይ ከገጠመ 3 ወር የመጨረሻው የመቀየሪያ ገደቡ እንደሆነ ብሔራዊ ባንኩ ይፋ አድርጓል።
የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ለለውጡ የሚሆን በቂ ገንዘብ አለኝም ብሏል።
ኢትዮጵያ በቀለም እና በይዘት የለወጠችውን የብር ኖት ለመቀየር 3.7 ቢሊየን ብር አውጥታለች ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዢ፤ የኢትዮጵያ ብር በጎረቤት ሀገሮች በከፍተኛ መጠን እንደሚገኝም ተናግረዋል።