የአሜሪካ 130 ሚሊዮን ዶላር እግድ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛትን የሚያስታውስ ነው ተባለ

የአሜሪካ 130 ሚሊዮን ዶላር እግድ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛትን የሚያስታውስ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፕሬዝዳንት ትራምፕ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ለኢትዮጵያ ሲሰጠው ከነበረው ደጋፈ ውስጥ 130 ሚሊዮን ዶላር እንዲታገድ ማድረጉ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ዘመንን የሚያስታውስ ነው ተባለ።

ሊዛ ቫይቭስ የተባሉ ተንታኝን ዋቢ ያደረገው ኢንዴፕዝ ኒውስኔት ድረገጽ፤ የድጋፍ እገዳው ካካተታቸው መርሃ ግብሮች መካከል የፀጥታ ድጋፍ ፣ የፀረ ሽብርተኝነት እና የወታደራዊ ትምህርት እና ስልጠና ፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ሲሆኑ ቅነሳዎቹ ለአስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፣ ለምግብ ዕርዳታ እንዲሁም ለ ኮቪድ-19 እና ለኤች.አይ.ቪ / ኤድስ የታለሙ የጤና ልማት እገዛዎችን እንደማያካትት ጠቁሟል።
የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ስለመቃረቡ የተናገሩት ተንታኟ፤ ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከመሆኑም በላይ ፣ጨ65 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኝ የሚያደርግና ለደቡብ ሱዳን ፣ ኬንያ ፣ ሱዳን ፣ ሶማሊያ እና ታንዛኒያም ሃይል የሚያቀርብ ነው ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
አሜሪካ የወሰደችው እርምጃ በኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂ ውስጥ በግልፅ ጣልቃ በመግባት ቅሬታን ስለመፍጠሩና የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስለመጋፋቱ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኙ ሎውረንስ ፍሪማንን እማኝ ያደረጉት ጸሐፊዋ ጉዳዩ ታዳጊ ሃገራት የህዝቦቻቸውን ህይወት ለመቀየር የሚወስዷቸው እርምጃዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች አካል ነው ሲሉ ገልጸውታል።
በ1959 ወንዙን በሚመለከት ስምምነት ሲደረግ ግብፅም ሆነ ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር እንደነበሩና ለግብጽም በአባይ ወንዝና ገባሮቹ ላይ ብቸኛ የባለቤትነት ስልጣን የሰጣት መሆኑንም ጸሐፊዋ አስታውሰዋል።
አባይን ለመቆጣጠር ወይም በብቸኛ ባለቤትነት ለመያዝ ሙከራ ከማድረግ ይልቅ፣ መተባበር ወቅቱን የሚመጥን እና ግድቡ የተገነባው ከኢትዮጵያውያን ድሃ ገበሬዎች በተሰበሰበ ገንዘብ እንጂ በዓለም ባንክ ድጋፍ ያለመሆኑን ጥቁር አሜሪካዊው የሰብአዊ መብቶች ተማጋች ጄሲ ጃክሰን ያብራሩበት ሠፋ ያለ ትንታኔም በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ተካቷል።

LEAVE A REPLY