ማንም አልተማረ || በማህሙድ እንድሪስ

ማንም አልተማረ || በማህሙድ እንድሪስ

ዘላለማዊ ህግ ብሎ እያረቀቀ
ማንም የማይሽረው ብሎ እያፀደቀ
እስከ ተለመው ግብ ማነው የዘለቀ ?
አንዱን እያላቀ
አንዱን እየናቀ
ዘመን ያዘመነው ጦር ስለታጠቀ
ባዲስ ቴክኖሎጂ ስለተራቀቀ
ባይደፈሬ አጥር ስለተጠበቀ
እስከ ምኞቱ ጥግ ማነው የዘለቀ?
እስክንድር ወደቀ
ሮማ ወደቀ
ቦናፓርት ወደቀ
ሂትለርም ወደቀ …
ሁሉም ወቅት አቆመው በጊዜው ተሻረ
ለሰው ልጅ መማሪያ ታሪክ ሆኖ ቀረ
ሆኖም ግን እስካሁን
ካሳለፍነው ታሪክ ማንም አልተማረ ።

LEAVE A REPLY