ማን እንደኔ እሪታ || ከወንዜው ማእበል

ማን እንደኔ እሪታ || ከወንዜው ማእበል

ሰበርናቸው ብሎ ሽመልስ ሲያቅራራ፣
ታኬ ‘ኮንዶ – በዘር’ ሲያድል በየተራ፣

ኢትዮጵያዊ ልቤ አዝናለች – ደምታለች
ምላሴ ግን ታጥፋ አንዲትም አላለች።
ይህንን በሽታ – ይህንን አባዜ፤ ባትወደውም ነብሴ:-
የሚይዝ ያዘና ዝም አለች ምላሴ፤
ከሌላ ሰፈር ግን ድምጽ የሰማሁ ለታ
አወይ የኔ ጩኸት፤ አወይ የኔ እሪታ
|| ከወንዜው ማእበል ||

LEAVE A REPLY