በ2022 ከኢትዮጵያ ተቃራኒ ሀሳብ ካላቸው የውጭ ሀገራት ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግነኙነት ይደረጋል 

በ2022 ከኢትዮጵያ ተቃራኒ ሀሳብ ካላቸው የውጭ ሀገራት ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግነኙነት ይደረጋል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፈረንጆቹ 2022 ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ እና ተቃራኒ አጀንዳ ካላቸው የውጭ ሀገራት ጋር ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መስራት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ያለፈው 2021 ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም ጫና የተደረገባት ዓመት እንደነበር ገልጸው ይሁን እንጂ በጠንካራ ሕዝቦቿ፣ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጥረት እና በተለያዩ አጋር የአፍሪካ ሀገራት ወገንተኝነት ጫናውን በመቀልበስ ኢትዮጵያ ማሸነፏን ተናግረዋል።

በዋናነት በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረው ጫና ኅዳሴ ግድብን እና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተወሰደውን ህግ የማስከበር እርምጃን እንደ ጭንብል በመጠቀም መሆኑን አመልክተዋል።

LEAVE A REPLY