ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተለያዩ ተቋማት እና ክረምት በጎፈቃደኞች አማካኝነት የታደሱ እና በአዲስ የተገነቡ 496 ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎችና አቅመ ደካሞች አስረከቡ።
ባለፉት ወራት በክረምት የበጎፈቃድ አገልግሎት መርኃግብር የተጀመሩ 315 ቤቶችን እድሳት በማድረግ እና 181 አዲስ የቀበሌ ቤቶችን በመገንባት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩና አቅመ ደካሞች ነው የመኖሪያ ቤቶቹ የተላለፉት፡፡
መረዳዳት እና መተጋገዝ የኢትዮጵያዊያን ባህል መሆኑን ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ ባስረከቡበት መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
በክረምት በጎ ፍቃድ መርኃግብርም የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራ የተሳተፉ ተቋማት፣ ግለሰቦችን እና ወጣቶችን አመስግነዋል፡፡