ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጥድፊያ የሚደረጉ ውሳኔዎች ፍትህን በመጨፍለቅ በተቋማቱ ላይ ያለንን እምነት በሂደት የሚሸረሽሩ ናቸው ተበዳይ ፍትህ ሳያገኝ እንዲሁም ሳይካስ በዳይን ነፃ ማውጣት በፍትህ ስርዓቱ መቀለድ፣ የሕዝባችንን ጉዳትም ማቃለል ነው በማለት የኢትዮጽያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ሁልጊዜ ወገንተኛነታችን ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ጋር ይሁን’ በሚል ባወጣው መግለጫ ፍትህ የአብሮ መኖር ማስተማመኛ ውል ነው ብለዋል።
በመንግሥት ታህሳስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም የተወሰደው እርምጃም ከሕዝብ ጋር ምክክር የጎደለው ግብታዊ እርምጃ እንዲሁም አመፀኝነትን የሚያበረታ እና መከፍፈልን የሚያጠነክር እጅጉን አሳሳቢ ተግባር ነው ብሏል።
በአሁኑ ሰዓት ትልቁ የሀገራችን አጃንዳ ከገባንበት ቅርቃር መውጫችን ሃገራዊ ምክክር ነው በማለትም የኢትዮጽያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ አሳስቧል።
ስለዚህም መንግስትና የመንግስት ሚድያዎች ለጉዳዩ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት አለመስጠታቸው ለታይታ ከሚደረጉ ነገሮች በዘለለ መላውን ህዝብ ያሳተፈ እዉነተኛ ምክክር እንዲደረግ ቆራጥነት እንደሚጎድል ማሳያ ነው በማለት የፓርቲው ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
በሀገራችን ያሉ ድምፆች ሁሉ መደመጥ እንዳለባቸው ብንገነዘብም ይህ አይነት የመንግስት ድርጊት በአጠቃላይ በሂደቱ ላይ ሊያሳድር እየፈለገ ያለውን ተፅዕኖ በግልፅ የሚያሳይ ሲሆን ከመሰል ተግባራት እንዲቆጠብ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ በማለት የመንግሥትን አካሄደ የተቸው የኢዜማ መገለጫ
መንግሰት የወሰደው እርምጃ አመፀኝነትን የሚያበረታ እና መከፋፈልን የሚያጠነክር እጅጉን አሳሳቢ ተግባር ነው፡፡ ከማለቱም በላይ መንግሥት ከዚህ ድርጊቱ መቆጠብ ብቻ ሳይሆን በይፋም ይቅርታ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ሲል አጽንዖት ስጥቷል።