ሰላም ባይኖርም ሰላም ልበላችሁ ውድ አንባቢያን፡፡
ነገሩ የተፈጸመው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012ዓ.ም ነው፡፡ ጀሞ ሁለት በሚባለው አካባቢ አንዲት አነስተኛ ቡና ቤትውስጥ የተከሰተ አስፀያፊ ድርጊት ነው፡፡ ባለቡና ቤቷለስምንት ዓመታት በሥራ ፍለጋ ያለ ሥራ ስትንከራተትቆይታ አክስት አጎቶቿ ተባብረው አንዲት ቡና ቤትይከፍቱላታል፡፡ በዚያ መተዳደር ከጀመረች ጥቂት ወራትአለፉ፡፡
ባፈው ቅዳሜ እንዲህ ሆነ፡፡ የሠፈር ሰዎች በቡና ቤቷደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ይዝናናሉ፡፡ የሚናገሩት በአማርኛነው፡፡ በአጋጣሚ ደግሞ የተከፈተው ዘፈን ተራው ሆኖአማርኛ ነው፤ ቡና ቤቶች ዘፈን እያፈራረቁ ነውየሚያዘፍኑት – በባለጊዜ ተረኞች ካልተገደዱ በስተቀር፡፡ ያኔ ያካባቢው ቄሮዎች ይሰባሰቡና “ሆ!” እያሉ መጥተው“ናፍጠኞታ! ናፍጠኞታ!” በማለት ቡና ቤቱን በድንጋይሩምታ ያደበላልቁታል፡፡ እንዲህ ያደረጉት ሴትዮዋ አማራመስላቸው ነው፡፡ እርሷ ግን በጊዜው አነጋገር ትግሬ ናት፡፡በትግሬነቷ ግን አልተጠቀመችም እንደመረጃ ምንጬ፡፡
ዕብዶቹ በድንጋይ ቡና ቤቱን ማተረማመስ እንደጀመሩሴትዮዋ ደምበኞቿን ገፋፍታ በጓሮ በር አስወጣችናየሚሆነውን ለማየት ቤቷ ውስጥ በድንገጤ ፈዝዛ ቁጭአለች፡፡ እነዚያ ቄሮዎች በኦሮምኛ አማራን እየተሳደቡናእየተራገሙ ፍሪጁን፣ በርና መስኮቶችን፣ በቤት ውስጥናበግቢው ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ ሰባብረውናየዘረፉትንም ዘርፈው ወደመጡበት ተመለሱ፡፡ አንድምገላጋይ አልነበረም፡፡ ሁሉም ለባለጊዜዎቹ ያጎበደደ ነውና፡፡
ሴትዮዋ ህግ ያለ መስሏት ልታመለክት ወደ ፖሊስ ጣቢያሄደች፡፡ እንደሄደች ላገኘችው ፖሊስ የደረሰባትን ግፍናበደል ስትነግረው በነገር ጥልልፍ ትግሬ መሆኗንያወቀው ፖሊስ በተሰባበረ አማርኛ “አንቺ ወያኔ ነሽኢንዴ… ነፍጠኛ አይደላሽ ኢንዴ… ነፍጣኛ ናትኮ ነውያሉት ልጆቹ፡፡ ላናጋሩ ሁለታቹም አንዲ ናቹ…ምንምሊናራግ አኒችልም…” በማለት አሹፎባትና ስቆባትአመናቅሮ እንደመለሳት የመረጃየ ምንጭ በምሬትገልጾልኛል፡፡ ይህ መረጃ በነገራችን ላይ የአካባቢው የቡናማጣጫ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አክራሪ ኦሮሞ ሀገራችንንእንዴት እየተጫወተባት እንደሆነ ከዚህ መረዳትይቻላል፡፡ ከሚዘገበው ደግሞ የማይዘገበው እጅግየበለጠ ነው፡፡
ይህች ናት ኢትዮጵያ፡፡ ነገሮች በብርሃን ፍጥነትእየተበለሻሹ ነው፡፡ የትናንትናው የነመረራ የትዳር አፍርሱጉዳይ ደግሞ እጅግ የሚገርም ነው፡፡ “አማራን ፈትታችሁእኔን አግቡኝ” የምትል ጉድ እንደተፈጠረች በግልጽእያየናት ነው፡፡ ይህ ሀፍረት የሚሉት ነገር በሀገር ጠፍቷል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡