ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ።
ሓላፊው አቶ ብርሃኑ ጣዕምያለው እንደገለጹት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በጤፍ፣ በበርበሬ እና በመድኃኒቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 724 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል።
በክልሉ መሰል ችግሮችን በመከታተል በዘላቂነት ለማስወገድ የሚያስችል ግብረ ሃይል መዋቀሩንም ተናግረዋል። የተለያዩ ሁኔታዎችን በመጠበቅ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እኔደሚቀጥልም ይፋ አድርገዋል።