ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአማራና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በመተከል እና አዊ ዞኖች የተፈናቀሉ የአማራና የጉሙዝ ማህብረሰብ አባላትን ወደ ቀደመ ቀያቸው ለመመለለስ እየተወያዩ ናቸው።
በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገ ጥሩነህ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸው ተነግሯል።
በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን እና በአማራ ክልል አዊ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ እና የቤንሻንጉል ማህበረሰብ አባላትን ወደ ቀደመ ቦታቸው ለመመለስ ያለመው ውይይት ከምን ስምምነት ላይ እንደተደረሰ እስካሁን ድረስ የታወቀ ነገር የለም።