22 መድኃኒት ቤቶና መደብሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ

22 መድኃኒት ቤቶና መደብሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሁለት መቶ ሠላሳ መድኃኒት ቤቶችና የመድኃኒት መደብሮችላይ በተደረገ ድንገተኛ ቁጥጥር በ22 ተቋማት ላይ እርምጃወስዷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ በሸቀጦች ላይምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትንየሚቆጣጠር ግብረ ሃይል መቋቋሙም ተገል ፡፡

ግብረ ሀይሉ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት መጋት 7 እና 8 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞችከፊት ጭምብልየእጅ ንፅህና መጠበቂያና ጓንት ጋር በተያያዘየተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ባላደረጉ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡ በ230 መድኃኒት ቤቶችና መደብሮች ላይ በተደረገ ድንገተኛየቁጥጥር ሥራ 22 ድርጅቶች ላይ ለመውሰድ አስችሏል፡፡

ምርቶችን በተጋነነ ዋጋ ሲሸጡ በተገኙ እና በድርጅታቸውውስጥ አቅርቦቱ እያለ የለንም ያሉ ሰባት ድርጅቶችማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ 15ቱ ደግሞ በቀጥታእንዲታሸጉ ተደርጓል፡፡

አንድ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያአስመጪና አከፋፋይ ጓንት መግዛት ለሚፈልጉ ደንበኞችሌሎች መድሃነቶችን ያለ ፍላጎታቸው ጨምረው እንዲገዙ በማድረጉ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒትቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY