ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትለአስራ አራት ቀናት በከፊል ሊዘጉ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እንደተናገሩት ፍርድ ቤቶቹ በከፊል የሚዘጉትከመጋት 10 እስከ መጋቢት 24 ነው፡፡
በነዚህ ጊዜያት ውስጥአዳዲስ መዝገቦች የማይከፈቱ ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ የዋስትና እናሌሎች አስቸኳይ ጉዳዮችና ከሀገር ፀጥታና ደህንነት ጋርየሚያያዙ ጉዳዮች ብቻ እየተመረጡ በተረኛ ችሎትእንደሚታዩም ተገልጿል፡፡