በወልቃይት ጠገዴ ዛሬ በአማራና የትግራይ የፀጥታ አካላት ዛሬ የተኩስ ልውውጥ ማካሄዳቸው ተሰማ

በወልቃይት ጠገዴ ዛሬ በአማራና የትግራይ የፀጥታ አካላት ዛሬ የተኩስ ልውውጥ ማካሄዳቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከማለዳ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ ፣ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እና የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ተሰማ።

ጉዳዮን አስመልክቶ ቢቢሲ የሁለቱንም የፀጥታ ኃይል ሓላፊዎች ሲያነጋግር አንዱ ሌላኛውን ክልል ቢወነጃጀሉም ችግሩ መኖሩን ግን አምነዋል።
በአማራ ክልል ሥር የሚገኘው የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ፤  እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ ምንም ግጭት አለመኖሩን ጠቁመው በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጸገዴ ወረዳ ግን ከምርጫው ጋር ተያይዙ ግጭት መኖሩን ገልጸዋል።
ስማቸው መግለፅ ያልፈለጉ  የትግራይ ክልል ፀጥታ ከፍተኛ ኃላፊም በምዕራብ ትግራይ ጸገዴ አካባቢ በትግራይ መሬት ገብቶ የተኮሰ አካል እንደሌለ በመጠቆም በአማራ ክልል ውስጥ ግን ተኩስ ነበረ ብለዋል።
የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳም  በትግራይ ደቡብ አካባቢ ምርጫውን የማደናቀፍ ሙከራዎች እንደነበሩ ጠቁመው፤ “በትግራይ ደቡብ አካባቢ ድንበር ላይ ግጭት ለማንሳት የሚሞክሩ ሰዎች አሉ። እኛም እነዚህ ትንኮሳዎችን ስንመክት ቆይተናል” ብለዋል።
ጉዳዮን በተመለከተ መግለጫ የሰጠው የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ የትምክህት ሃይሎች  አካላት ከምርጫ ጣቢያ ራቅ ባለ አካባቢ ትንኮሳ አድርገዋል ከማለቱ ባሻገር፤
“በቂ ሃይል ስላለ ትንኮሳው አልተሳካም። ሙከራው ለደቂቃዎች ብቻ እንደነበረም ለማወቅ ችለናል”  ሲል በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክብረዓብ ቸርነት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው የጸገዴ ወረዳ ውስጥ ልዩ ስሙ ጨቋር ኩዶቢን በሚባል ቦታ፣ ከሌሊቱ 8 ሰዐት አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ነዋሪው ወጥቶ እንዲመርጥ እንዲሁም ሚሊሻው ደግሞ “አማራ ሊወርህ እየመጣ ስለሆነ መንገድ ዝጋ” የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር ብለዋል።
ይሁን እንጃ ሕዝቡ የመምረጥም ሆነ መንገድ የመዝጋት ፍላጎት አልነበረውም ያሉት አቶ ክብረዓብ ሕዝቡ ምላሽ ባለመስጠቱ ችግሩ እንዳልተባባሰና ከተኩስ ልውውጥ የዘለለ የከፋ አደጋ አለመከሰቱን ገልጸዋል።
የህወሓት የፀጥታ ኃይሎች ሕዝቡን ለምርጫ ካርድ በግዴታ እንዲወስድ ሲያስጨንቁ መሰንበታቸውንና የምርጫ ካርድ አልወሰዳችሁም በሚል ከቀናት በፊት ከ500 በላይ ወጣቶችን እየደበደቡ ወስደው ማሰራቸውን፣ በተመሳሳይ ዛሬም አካባቢውን ሲያሸብሩ መዋላቸውን የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ተወካዮ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY