ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ካለባቸው የዓለም ሀገራት ዐሥረኛ ደረጃን ያዘች

ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ካለባቸው የዓለም ሀገራት ዐሥረኛ ደረጃን ያዘች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የተማረ የሰው ሀይል እጥረት ያለባቸው ዐሥር ሃገራት ይፋ ተደረጉ።

የተማረ ሀይል እጥረት ካለባቸው ሃገራት፤ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት በመቶኛ ዐሥር ሀገራትን ያስቀመጠው ጥናት አፍሪካዊያን በዚህ ችግር የተበተቡ መህናቸውን አመላክቷል።
በዚህም መሠረት ቡርኪናፋሶ 36 በመቶ በመሆን አንደኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠች የጠቆመው ጥናት፤ ከቡርኪና ፋሶ በመቀጠል ሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ እና አፍጋኒስታን ሁለተኛ እና ሦተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፤ ቤኒን እና ማሊ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ 38.4 ፣38.7 የሆነ ተቀራራቢ ቁጥር በማስመዝገብ በዝቅተኛ የተማረ የሰው ሀይል ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡
አሁን ላይ የተማረ የሰው ሀይል እጥረትን ለመቅረፍ ደፋ ቀና እያለች መሆኑን የገለጸችው ኢትዮጵያ በዝርዝር ጥናቱ ውስጥ ዐሥረኛ ደረጃን ይዛለች።

LEAVE A REPLY