ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ዋና መዲና የሆነችው አዲስ አበባን የማስዋብ አንዱ አካል የሆነው የሸገር ባርክ የወዳጅነት አደበባይ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቋል።
ይህ ፓርክ ከእንጦጦ ፓርክ እስካ ባምቢስ ድልድይ እየተሰራ ያለው ሸገርን የማስዋብ የ12 ኪሜ ፕሮጀክት አካል መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ፤ ግንባታው በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡
ዛሬ ምረቃው የተካሄደው ፓርክ በቻይና የኮንስትራክሽን ድርጅት እየተገነባ ይገኛል። በፓርኩ የምረቃ ሥነሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ሌሎች በፕሮጀክቱ ላይ በተለያየ መልኩ የተሳተፉ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ወታደራዊ ትእይንት በማቅረብ ፕሮግራሙን ድምቀት ሰጥተውታል።