አቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ የፀረ ሽብር አዋጅን ተላልፈዋል በሚል ክስ...

አቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ የፀረ ሽብር አዋጅን ተላልፈዋል በሚል ክስ መመሥረቱ ታወቀ።

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከጀምሩ የእስሩ ጉዳይ አነጋጋሪ የሆነው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ የፀረ ሽብር አዋጅን ተላልፈዋል በሚል ክስ መመሥረቱ ታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የታከለ ኡማ አስተዳደር የፊንፊኔ ኬኛ ፖለቲካን ያራምዳል በሚል ከስርዓቱ ጋር ግልፅ ውዝግብ ውስጥ የገባው በፖለቲከኛና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የቀረቡት ክሶች ኃይልን በመጠቀም መንግሥትን ለመቆጣጠር ሙከራ አድርጓል የሚል መሆኑ ደግሞ ብዙኃኑን ኅብረተሰብ እያነጋገረ ይገኛል።
ዛሬ ሐሙስ ጠዋት  እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ፈጽሞ እንደማያውቅና አካልን ነፃ ለማውጣት በከፈተው የክስ መዝገብ ለከሰዐት ቀጠሮ የነበረው በመሆኑ እርሱን ሲከታተል በድንገት ያለጠበቃ ፍርድ ቤት መቅረቡን ኢትዮጵያ ነገ አረጋግጧል።
ፍርድ ቤት በፖሊስ ከተወሰደ በኋላ የክስ መዝገብ የተሰጠው ሲሆን፤   “የጦር መሳሪያን በመጠቀም የመንግሥትን ሥልጣን ለመቆጣጠር አመፅ በመፍጠር” እና “የፖለቲካ ዓላማን ለማራመድ በመስማማትና ሕዝብ በማሳመጽ የሽብር ተግባር በመፈፀም መንግሥትን በኃይል ለመቆጣጠር” የሚሉ ክሶች እንደተመሰረተበት ታውቋል።
አነጋጋሪ ነው በተባለለት በዚህ የክስ መዝገብ ነተከሰሱት ሰባት ሰዎች ሲሆን አራቱ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። ከጠበቃው ባገኘነው መረጃ መሠረት ሁለቱም ክሶች በእስክንድር ላይ የቀረቡ ሲሆን፤ በሌሎቹ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ላይ ግን የተመሰረተው አንድ ክስ ብቻ እንደሆነ ታውቋል።

LEAVE A REPLY