ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፥ በኢትዮጵያ ቁልፍ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ከእስር መፈታታቸውን በደስታ እቀበላለሁ ብለዋል።
የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲቆምና ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ ፣ እንዲሁም ተአማኒና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይትና የእርቅ ሂደት እንዲጀመር በመስማማት ይህን ትልቅ የመተማመን ግንባታ ሂደት እንዲያጎለብቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
መንግስት ከእሥር በምሕረት እንዲፈቱ መወሰኑን ያስታወቀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አቶ ስብሐት ነጋ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ አቶ ዓባይ ወልዱ አቶ አባዲ ዘሙ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር አቶ ኪሮስ ሐጎስ አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ መንግስት ማስታቁ የሚታወስ ሲሆን ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም እና ሰላምና መረጋጋትን ወደነበረበት ለመመለስ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በንቃት እሰእሰራለሁ ብሏል