ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የራሳቸው ተከታይ ያላቸው የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንም ሆነ ሌሎች በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በዕስር የነበሩ አካላትን የክስ ሂደት ማቋረጡ እንደሀገር ሊደረግ ለታሰበው ሁሉን አቀፍ እና አካታች ብሄራዊ ምክክር ምቹ መደላድል የመፍጠር ሚናው ትልቅ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።
መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ በርካቶች ፤እየታቃዎሙት ሲሆን የማህበረሰብ አንቂዎች የመንግስት ዳጋፊ የነበሩ አክቲቪስቶች አሶሻል ሚዲያ በመቃወም ላይ ናቸው ።
ነገር ግን አንድ አንድ የአለም አቀፍ ተቋማት መንግስት የወሰነው ውሳኔ ደስተኛ መሆናቸው እየገለፁ ይገኛሉ በትናንት እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ መደሰታቸውን መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ሙሳ ፋኪ አክለውም በሀገራዊ ምክክሩም ሁሉም አካላት ሊሳተፉ እንደሚገባ እና የአፍሪካ ህብረትም ለምክክሩ ስኬታማነት የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ ጠንክሮ እንደሚሰራ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል።