በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ከሚገኙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ 115ቱ እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቢ...

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ከሚገኙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ 115ቱ እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለጸ

የዶክተር መረራ ጉዲና ክስ መቋረጡን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ጌታቸው አምባየ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ክሳቸው የሚቋረጠውና ይቅርታ የሚደረግላቸው እስረኞች 115 ብቻ መሆናቸውን ገለጹ።የሂደቱን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆነ በጸረ-ሽብር ህጉ የተከሰሱትንም እንደሚጨምር ገልዋል።

በመጀመሪያው ዙር የሚፈቱት እሰረኞች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት እንዳለባቸውም ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ገልጸዋል።

ህገ-መንግሥቱን ወይም ህገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን የመናድ እንቅስቃሴ ላይ ያልተሳተፉ ወይም ያልመሩ፤በከፍተኛ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ጉዳት ለማድረስ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ያልተሳተፉ ወይም ያልመሩ፤ የሰው ህይወት ያላጠፉ ወይም በአካል ላይ ከባድ ጉዳት ያላደረሱና በስርዓቱ ተጠቃሚ ሆነው ሳለ በሌሎች ገፋፊነት ወደ ሁከት እና ብጥብጥ የገቡ እስረኞች ከሁለት ቀናት የተሃድሶ ስልጠና በኋላ ይፈታሉ ብለዋል።

ጠቅላይ አቃቢ ህጉ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የሚፈቱት እስረኞች 528 ሲሆኑ 413ቱ ከደቡብ ክልል ናቸው ብለዋል።በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥም ስም ዝርዝራቸው ይፋ ይሆናል ተብሏል።

ዥንዋ ኔት የታበለ የድረ-ገጽ ጋዜጣ እ.ኤ.አ ታህሳስ 25/2017 የደቡብ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሰይፉ ከነሶን ጠቅሶ በሰራው የዜና ዘገባ በጌዲዮ ዞን በ2016 በተፈጠረው ግጭ ከተሳተፉት መካከል 361 እስረኞች በክልሉ መንግስት ምህረት ተደርጎላቸው መፈታታቸውን ዘግቦ ነበር። አሁን የፌዴራል አቃቢ ህግ ይፈታሉ ካላቸው መካከል ይሁኑ አይኑ ለጊዜ ማወቅ አልተቻለም።

LEAVE A REPLY