የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ ቁጥር 1

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ ቁጥር 1

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 1 አንድ ይፋ ሆኗል። ከኮማንድ ፖስቱ ውጭ የፌዴራልም ሆነ የክልል የመንግስት አካል በፀጥታ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጡ ከልክሏል።ይህ ደግሞ መፈንቅለ መንግስት ነው።በግልፅ ያልታወጀውም ሁኔታዎች ሲረጋጉ የህወሓት የበላይነት ለሰፈነበት ስርዓት መልሶ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው።የተጨቆነ ህዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አያስቆመውም።ህዝቡ የህወሓትን የድንጋይ ዘመን ሰዎች ላለመገዛት እምቢ ብሏል።

ህዝቡ እምቢ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሁለት አይነት መመሪያዎች እንዳሉት ተገልጿል።መመሪያ ቁጥር አንድ የሚከተለው እንደሆ ይፋ ተደርጓል።

——————————

1. በመላው ሀገሪቱ የሚተገበሩ ክልከላዎች

1.1 ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የሚጥስ ተግባር መፈፀም፥

በመመሪያው መሰረት ማንኛውም ሰው በሀይል፣ በዛቻ እና በየትኛውም መልኩ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የሚጥስ ተግባር መፈፀም የለበትም፤ የጦር መሳሪያ ይዞ ማመፅ እና የእርስ በእርስ ግጭት እንዲኖር መፍጠርም ክልክል ነው።

1.2 የህዝቡን አንድነትና መቻቻል የሚጎዳ ተግባር መፈፀም

1.3 ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ እና መደገፍ

1.4 የትራንስፖርት እንስቃሴን ማወክ

1.5 የህዝብ አገልግሎት ማስተጓጎል፣ ማቋረጥ እና መዝጋት

1.6 የመሰረት ልማት ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረስ

1.7 የህግ አስከባሪዎችን ስራ ማወክ

1.8 ያልተፈቀደ ሰልፍ እና የአደባባይ ስብሰባ ማድረግ

1.9 በትምህርት ተቋማት አድማ ማድረግ

1.10 በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አድማ ማድረግ

1.11 ሁከትና ብጥብጥ የሚያነሳሳ ቅስቀሳ እና ግንኙነት መፍጠር

1.12 የመሰረታዊ ሸቀጦችን ዝውውር ማወክ

1.13 ባህላዊ፣ ህዝባዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ብሄራዊ በዓላትን ማወክ

1.14 በገበያ፣ ሀይማኖታዊ ተቋማት፣ በዓላት እና ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ የጦር መሳሪያ ይዞ መግባት

1.15 የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችን ማድረግ

1.16 ከኮማንድ ፖስቱ ውጭ በፀጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት

አዋጁንና አዋጁን ተከትለው የወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን አስመልክተው የሚከለክሉ ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል፡፡

እነዚህን ክልከላዎች በመላ ሀገሪቱ የሚተገበሩ ክልከላዎች ናቸው።

2 በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚተገበሩ ክልከላዎች

2.1 የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ

የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ይፋ በሚያደርጋቸው ስፍራዎች የትኛውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ አይፈቀድም

2.2 የሰዓት እላፊ ገደብ

የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ይፋ በሚያደርጋቸው ስፍራዎች የሰዓት እላፊ ገደብ ያስቀምጣል፡፡

በትላልቅ ፋብሪካዎች፣ በኢንዱስትሪ ማዕከላት በሰፋፊ እርሻዎች የሰዓት እላፊ የሚጣልባቸው ስፍራዎች ናቸው።

2.3 የዜጎችን ደህንነት በተመለከተ

የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ዜጎችን በአንድ በተወሰነ ስፍራ ማቆየት፤ ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ማዘዋወር

2.4 ለአካባቢ ስጋት ሲባል ወደ ተዘጋ መንገድ መግባትን መከልከል፡፡

3 የመተግበር እና የማሳወቅ ግዴታ

3. 1 የቤትና የተሽከርካሪ አከራዮች

የተከራይን አካል ማንነት መዝግቦ በግልፅ መያዝ፣ በፅሁፍ የሰፈረውን መረጃ በ24 ሰዓት ውስጥ ለፖሊስ ማሳወቅ፣ ተከራዩ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ የተከራዩን ፓስፖርት እና የኪራይ ውል ለፖሊስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

3.2 መረጃ የመስጠት ግዴታ

ማንኛውም ተቋም በተጠየቀበት ጊዜ ለህግ አስከባሪ አካል መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት።

3.3 ማንኛውም ሰው የኮማንድ ፖስቱን ውሳኔ የማክበር እና የመተግበር ግዴታ አለበት።

4 እርምጃዎች

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፎ መገኘት እርምጃዎችን ያስወስዳል።

የሚወሰዱ እምጃዎችም ፦

ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል

በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎችን ኮማንድ ፖስቱ በወሰነው ቦታ እንዲቆዩ ይደረጋል፤

ማንኛውም ስፍራ እና አካል ላይ በማንኛውም ሰዓት ብርበራ ማድረግ፤

የተዘረፉ ንብረቶችን አጣርቶ ለባለቤቶቹ መመለስ፤

በትምህርት ተቋማት ረብሻ የሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዝ።

5. የሀይል አጠቃቀም

የህግ አስከባሪ አካላት እና የጥበቃ ሀይሎች የራሳቸውን ደህንነት መጠበቅ ይችላሉ።

የዜጎችን ደህንነት እና የኢንቨስትመንት ተቋማትን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው።

ይህንን ግዴታቸውን ለመወጣት ተመጣጣኝ ሀይል መጠቀም እንደሚችሉም በመመሪያው ተደንግጓል።

LEAVE A REPLY