የመከላከያ ሰራዊት በሞያሌ ከተማ ባካሄዱት የጅምላ ጭፍጨፋ የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ

የመከላከያ ሰራዊት በሞያሌ ከተማ ባካሄዱት የጅምላ ጭፍጨፋ የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በወያኔ ጦር ጄኔራሎች የሚመራው መከላከያ ሰራዊት በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በህዝብ ላይ በድገት በከፈተው ጭፍጨፋ የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ።በሞያሌ ከተማ ዛሬ እኩለ ቀን በሰራዊቱ በተከፈተ ተኩስ 13 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ22 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በጽኑ ቆስለው በሞያሌ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።

መከላከያ ሰራዊት የጅምላ ጭፍጨፋ ያካሄደው ዛሬ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ ምንም አይነት የህዝብ ተቃውሞ ባልነበረበት በሆቴል ምሳ ሲመገቡ የነበሩና አስተናጋጆች እንዲሁም በመንገድ ላይ ሲያልፉ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎች ግድያ መፈጸሙን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ሞያሌ ከተማ በቦረና ዞን ስር የምትገኝ ሲሆን ኦሮሚያና ኢትዮ-ሶማሌ ክልሎች በወሰን ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ለዓመታት የዜጎች ህይወት በተደጋጋሚ ሲጠፋ መቆየቱ ይታወቃል።

ለ27 ዓመታት ከተማዋ በአወዛጋቢ ሁኔታ በሁለቱ ክልሎች ስትመራ የቆየች ሲሆን ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ በመግባት እያስተዳደራት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ባደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY