እስክንድር ነጋ

 /ክንፉ አሰፋ/

እስክንድር ነጋ

 /ክንፉ አሰፋ/

ክንፉ አሰፋ — አምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር ለክብር እንግድነትበሆላንድ የጠራው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሊወጣ ሲል በህወሃት ታግቷል። 
ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል።

የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም። እስክንድር ነጋ ሃሳቡን በነጻ በመግለጹ ምክንያት የመጨረሻውን ሳንደምረው ለ8 ጊዜ ታስሯል። እ. ኤ. አ, በ 2013 በሽብርተኝነት ተከሶ 18 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር።

እስክንድር ነጋ የካቲት 14 ቀን 2018 ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጋር ቢለቀቅም እንደገና ለ 9ኛ ጊዜ ታሰሮ ነበር።
እስክንድር ከዘጠኝ በላይ የክብር ሽልማቶች ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው።

1. በ 2011 PEN America (NY,)


2. በ 2012 Barbara Goldsmith Freedom to Write Award

3. በ 2014 World Association of Newspapers’ Golden Pen of Freedom Award

4. በ 2015 PEN Canada Freedom of Expression Award

5. በ 2017 International Press Institute World Press Freedom Hero

6. በ 2018 Oxfam Novib/PEN Award for Freedom of Expression (60 laureates)

7. ሂዩመን ራይት ዋች የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና አምነስቲ የኢንተርናሽናል የክብር ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ነው።
 ዶር አብይ አህመድ ለውጥ ሊያመጣ ቃል በገባ ሳምንታት ቢቆጠሩም የህወሃት አፈና እና ግድያ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የአለም መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

ዛሬ በ እስክንደር ነጋ ላይ የተፈጸመው የተለመደ የህወሃት በደል በዶ/ር አብይ ፈንጥቆ የነበረውን ተስፋ የሚያጨልም ነው። የህግ ሳይሆን የህወሃት የበላይነት እስካለ ድረስ በአኢትዮጵያ ለውጥ አይታሰብም።

ሕወሃት አይታደስም። አይተገንምም። ህወሃት ከምድሪቱ ላይ መጥፋት ነው ያለበት። ይህ ደግሞ በሕዝባዊ አመጹ እውን ይሆናል።
 እስክንድር ነጋ በሆላንድ ሃገር ከተዘጋጀለት የአምነስቲ ዝግጅት በኋላ ልጁን እና ባለቤቱን ለማየት ወደ አሜሪካ ሊያመራ እንደነበር ይታዋቃል።

የሆላንድ ንጉስ ዊለም አሌክሳንደር የሚገኙበት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ከብረ-በዓል በእስክንድር ያለመገኘት የተነሳ መልካም የነበረ ድባቡ እንዲጠፋ መደረጉን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተወካይ ገልጸውልናል።

LEAVE A REPLY