/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ፖስፖርት የነጠቁ የደህንነት አባላት ከስራ መታዳቸው ተገለጸ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ትናንት ሌሊት ወደ ውጭ ሀገር ጉዞ ለማድረግ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፓስፖርቱን የነጠቁ የቦሌ ኢምግሬሽን ሰራተኞች ከስራ መባረራቸውን ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ገልጿልች። እስክንድርም በሆላንድ አምስተርዳም በሚከበረው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ በዓል ላይ ለመገኘት ጉዞ መብረሩንም ጨምራ ገልጻለች።
ጋዜጠኛ ሰርካለም የሚከተለውን በፌስ ቡክ ገጿ አስፍራለች፦
“እስክንድር ነጋ ወደውጭ በረራውን አድርጓል
“ጉዳዩ ከከፍተኛ ሀላፊዎች እውቅና ውጭ ነው”
እስክንድር ነጋ ትላንት በረራው የተስተጓጎለው ከከፍተኛ ሃላፊዎች እውቅና ውጭ ነው ሲሉ የቦሌ ኢምግሬሽን አንድ ሃላፊ ነግረውናል። እስክንድርን ለደረሰበት መጉላላት በአክብሮት ይቅርታ ጠይቀን ወደውጭ ሸኝተነዋል ሲሉም ሃላፊው በስልክ ነግረውኛል። ለመሆኑ ይህንን ጥፋት ባጠፉት ሰራተኞች ላይ ምን እርምጃ ወሰዳችሁ በሚል ላነሳሁላቸው ጥያቄ ሃላፊው በሰጡት ምላሽ ይህን ያደረጉ ሰራተኞች ለጊዜው ከስራ እንደታገዱና በቀጣይም ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ገልፀው; ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለንም ብለዋል።
ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉት ይህ የቦሌ ኢምግሬሽን ሃላፊ “እስክንድር ዛሬም አልተፈታም ማለት ነው”በሚል በፌስበክ ገፄ ላይ የፃፍኩትን በመመልከት እጅግ ወዳጄ በሆነ ሰው በኩል አግኝተው ነው መረጃውን የሰጡኝ።
ለማንኛውም ወዳጃችን እስክንድር እንኳን ያሰብከው ተሳክቶ ጉዞህ ሰመረ እላለሁ ደስ ብሎኛል!!!”