/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ካናዳ ውስጥ በተፈፀመ የተሽከርካሪ ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ። በቶሮንቶ ከተማ አንድ ግለሰብ በእግረኞች መንገድ ላይ በመግባት በመኪና በፈፀመው ጥቃት 10 ሰዎች ሲሞቱ ከ16 በላይ መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የጥቃቱ ፈፃሚ ግለሰብ አሌክ ሚናሲያን የተባለ የ25 ዓመት ወጣት መሆኑንና በቁጥጥር ስር የዋለው ጥቃቱ ከተፈፀመበት ስፍራ ርቆ እንደሆነም ፖሊስ ታውቋል።
የቶሮንቶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ጥቃቱ ሆን ተብሎ የተፈፀመ ቢሆንም ምክንያቱ ግን እስካሁን ምን እንደሆነ አልታወቀም ብለዋል። መኪና ተከራይቶ ጥቃት የፈፀመው ሚናሲያን የቶሮንቶ ከተማ ነዋሪም እንደነበር ተገልጿል።
ተሽከርካሪን በመጠቀም በእግረኞች ላይ ጥቃት መፈፀም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በካናዳ፣ አሜሪካና አውሮፓ ሀገራት እየተለመደ መጥቷል።