ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ነፃነት አሁንም ከመጨረሻዎቹ ታርታ ናት ተባለ

ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ነፃነት አሁንም ከመጨረሻዎቹ ታርታ ናት ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ነፃነት አሁንም ከመጨረሻዎቹ ታርታ ላይ ናት ተባለ። በኢትዮጵያ ስራ ላይ የዋለው የ“ፀረ-ሽብርተኝነት” አዋጅ ለመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ፈተና ሆኖ መቀጠሉን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ።

በቀመጫውን በፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው ሪፖርተር ዊዝ አውት ቦርደርስ (Reporters Without Borders ) የ2018 የአለም ሀገራትን የሚዲያ ነፃነት ደረጃ ጠቋሚ ሪፖርት ዛሬ ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራት 150ኛ ላይ አስቀምጧታል። በኢትዮጵያ በ2001ዓ.ም የታወጀው የ“ፀረ-ሽብርተኝነት” አዋጅ ለሀገሪቱ የሚዲያ እድገት ከፍተኛ ፈተና እየሆነ መምጣቱንም ሪፖርቱ አትቷል።

መንግስት የፀረ-ሽብር አዋጁን በመጠቀም በርካታ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን፣ጋዜጦችና መጽሄቶች መዘጋታቸውንና በየጊዜው ጋዜጠኞች መሰደዳቸውን ጠቅሷል። ኢትዮጵያ በየጊዜው የምታወጣቸው ህጎች የመናገርና የመጻፍ መብትን የሚገድቡ መሆናቸውን የድርጅቱ መግለጫ አመልክቷል።በሀገሪቱ የተጣለው የአስጀኳይ ጊዜ አዋጅም ሁኔታውን እያባባሰው መምጣቱን ጠቅሷል።

በRSF የአለም የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት መረጃ ጠቋሚ (World Press Freedom Index) መሰረት ኖርዌይ 1ኛ፣ ስዊዲን 2ኛ፣ ኔዘርላንድ 3ኛ የሚዲያ ነፃነት ያለባቸው ሀገራት ሲሆኑ ሰሜን ኮሪያ 179ኛ እንዲሁም ኤርትራን መጨረሻ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

LEAVE A REPLY