አሁኑኑ ሊያነቡት የሚገባ-ዶላሩና አጭሩ ዲፕሎማት! /ስዩም ተሾመ/

አሁኑኑ ሊያነቡት የሚገባ-ዶላሩና አጭሩ ዲፕሎማት! /ስዩም ተሾመ/

እንዲህ ሆነ! በምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳለው የሚነገርለት ቁመተ አጭሩ አሜሪካዊ ዲፕሎማት ያማማቶ አዲስ አበባ መጣ፡፡

የያማማቶ ዋና ትኩረት በደቡብ ሱዳን መሪዎች ላይ ስለሚጣለው ማዕቀብ የኢትዮጲያን መሪዎች ለማማከር ነበር፡፡ አያይዘውም ማዕቀብ የሚጣልባቸው መሪዎች በራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም በውጪ ሀገር በሚገኙ ባንኮች የከፈቱትን አካውንትና ያስቀመጡትን የገንዘብ መጠን በቀላሉ ማወቅ እንደሚቻል ይገልፃሉ፡፡

ይህን ግዜ ጠ/ሚ አብይ “ቆይ…ቆይ እኛ የተቸገርነው ይሄን አይደለም እንዴ?” በማለት በተመሣሣይ መንገድ የኢትዮጲያ ባለስልጣናት በየትኛው ሀገር የባንክ አካውንት እንዳላቸውና ያጠራቀሙትን የገንዘብ መጠን የሚያሳይ መረጃ በማሰባሰብ እንዲያግዟቸው ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ያማማቶ ደግሞ እኔ ምን ገዶኝ በማለት የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናትን ጉድ በCIA በኩል ጎልጉለው እንሆ በረከት ይሏቸዋል፡፡

ከደሃው የኢትዮጲያ ህዝብ ላይ የተዘረፈው ብር በአንደኛ ደረጃ የሚገኘው በጀርመን ሀገር እንደሆነ ታወቀ፡፡ ከሚታወቁት ቱባ-ቱባ የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በላይ ኤልክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ዋና ሃላፊ የሆነችዋ ሴትዮ $180,000,000 ዶላር በውጪ ሀገር ባንክ ማስቀመጧ ሁሉም አስገርሟል፡፡

ይህቺ ጀማሪ ባለስልጣን 180 ሚሊዮን ዶላር ከዘረፈች ነባሮቹ ምን ያህል እንደሚዘርፉ መገመት ይቻላል፡፡

LEAVE A REPLY