የዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ሐውልትና የሴቫስቶፖል መድፍ ዕድሳት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ

የዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ሐውልትና የሴቫስቶፖል መድፍ ዕድሳት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ሐውልትና የሴቫስቶፖል መድፍ ዕድሳት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ሐውልትና የሴቫስቶፖል መድፍ በአምስት ሚሊዮን ብር ወጭ ዕድሳት ዕድሳት እየተደረገለት ሲሆን በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ቢሮው አስታውቋል።

እንደ አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ገለፃ ከሆነ ቅርሶቹ እየታደሱ ያሉት የቀድሞ ቅርጽና ይዘታቸውን በጠበቀ ነው ተብሏል። አንድ አካላት ዕድሳት የሚደረገው በሲሚንቶና ኮንክሪት ነው የሚሉትም ውሸት ነው ሲል ባህልና ቱሪዝም ተናግሯል።

የፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ደግሞ በጥናቱ መሰረት እየታደሱ ስለመሆናቸው  አራት “ጥራት ተቆጣጣሪ”  ባለሙያዎችን መድቦ እየተከታተለ መሆኑንም ባህልና ቱሪዝም ቢሮን ጠቅሶ አማራ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

 

LEAVE A REPLY