ኦህዴድ ወደ ህብረብሔራዊ ድርጅት ሊያድግ ነው የተባለው ሀሰት ነው ተባለ

ኦህዴድ ወደ ህብረብሔራዊ ድርጅት ሊያድግ ነው የተባለው ሀሰት ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦህዴድ) ስያሜዉን ወደ የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢህዴድ)  በመቀየር  ከብሄራዊ ድርጅትነት ወደ ህብረብሄራዊ ድርጅት ሊቀየር ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሀሰት መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ አስታወቁ።

የኦህዴድ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት “የደረስንበትን የትግል ምዕራፍ ከግንዛቤ በማስገባት  በመጪዉ ነሐሴ ወር በሚያካሄደዉ ድርጅታዊ ጉባዔ የስያሜ፣ የዓርማና ድርጅታዊ መዝሙሩን በአዲስ ሊቀይር  የሚችል ቢሆንም ብሔራዊ ድርጅት ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል።” ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ አዲሱ ጉዳዩን በማስመልከት በፌስ ቡክ ገፃቸው የሚከተለውን አስፍረዋል።

_________

“የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስያሜዉን ወደ “የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት” (ኢህዴድ) በመቀየር ከብሄራዊ ድርጅትነት ወደ ህብረብሄራዊ ድርጅት ሊቀየር ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሀሰት ነዉ። ሆኖም ኦህዴድ እንደአስፈላጊነቱ የደረስንበትን የትግል ምዕራፍ ከግንዛቤ በማስገባት በመጪዉ ነሀሴ ወር በሚያካሂደዉ ድርጅታዊ ጉባዔ የስያሜ፣ የዓርማ እና ድርጅታዊ መዝሙሩን በአዲስ ሊቀይር የሚችል ቢሆንም ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል።”

LEAVE A REPLY