/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ብፁዕዎ ቅዱስ ፓትርያርክ አባ መርቆሪዮስ ለቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ይቅርታ ማድረጋቸው ተገለጸ።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ ከ26 ዓመታት በፊት ሀገራቸውንና መንበራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ የገፏቸውን ብፁዕዎ ቅዱስ ፓትርያርክ አባ መርቆሪዮስን ይቅርታ ጠየቁ።
በፁዕ ቅዱስ ፓትርያርክ አባ መርቆሪዮስም ለአቶ ታምራት ላይኔ ለሰራው ስህተት በአባትነታቸው ይቅር ማለታቸውን ከቤተክርስቲያኒቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
አቶ ታምራት ላይኔ ቅዱስ ፓትርያርክ አባ መርቆሪዮስን ከሀገር እንዲወጡ ያደረኩት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ታዝዠ ነው በማለት ከቀናት በፊት ከናሁ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ_ምልልስ መግለፃቸው ይታወሳል።