👉የእነ ኮሚሽነር የእቆብ ሸራተን መዝገብ የሚያካትተው፤ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩትን አንደኛ ተከሳሽ ኮሚሽነር ያእቆብ ሸራተንን ጨምሮ ሌሎች 16 በክልሉ በተለያየ ስልጣን ላይ የነበሩ በአጠቃላይ 37 ተከሳሾች ናቸው።
👉በጋምቤላ ክልል በ2006 መጨረሻ ላይ የተከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት አነሳስታችኋል ፤ በግጭቱ ምክንያትም ለጠፋው የሰው ህይወት እና ንብረትም ተጠያቂ ናችሁ ተብለው ነው ክሱ በታህሳስ ወር 2007 የተመሰረተባቸው።
👉ከ37ቱ ተከሳሾች ውስጥ 13ቱ ሰው በመግደል ወንጀልም ተጨማሪ ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው።
👉ተጠርጥረው ከታሰሩበት መስከረም ወር 2007 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በእስር ሆነው ክሳቸውን እየተከታተሉ ነው።
👉አራት አመት ለሚጠጋ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ ከ17 በላይ ዳኞች እና አቃቤ ህጎች እንደተቀያየሩባቸው አሁን ላሉት ዳኞች ተናግረዋል። ወደ ክልላቸው ወይም አቅራቢያ ቦታ እንዲዳኙ ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት አላገኘም።
👉32ኛ ተከሳሽ የነበረው ሰለሞን ኑራኪ በእስር ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል።
👉 4ት ተከሳሾች መጋቢት 19/2009 በተሰጠው ብይን በነፃ ተሰናብተዋል።
👉 በግጭቱ ምክንያት ተጣልተው የነበሩት ህዝቦች እርቅ ማውረዳቸውን በመጥቀስ ክሳቸው እንዲቀር ወይም በማቅለያነት እንዲያዝላቸው አቤቱታ አቅርበው ነበር።
👉 ግንቦት 9/2010 በተሰጠው ፍርድ 3ት ተከሳሾች ነፃ ሲወጡ የተቀሩት 29ኙ ጥፋተኛ ተብለዋል።
👉 ዛሬ በነበራቸው ቀጠሮ በምህረት አዋጁ መሰረት መፈታት አለብን ብለው ባመለከቱት መሰረት ምላሽ ለመስማት ነበር። ሆኖም ዛሬም አቃቤ ህግ ምላሽ ባለማቅረቡ ለሰኞ ሃምሌ 30/2010 ከሰአት የጠቅላይ አቃቤ ህግ አዋጁ የሚመለከታቸውን እና የማይመለከታቸውን በተመለከተ አፈፃፀሙን በፅሁፍ እንዲያቀርብ ዳኞች አዘዋል።
👉23ኛ ተከሳሽ ከድር አብዱራህማን ዛሬ የሰጠው አስተያየት 👉 “ከኛ በኋላ በኮንሶ እና በጌዲዮ ግጭት የታሰሩ ተፈተዋል። ለእኛም ለህጉም ስትሉ አፋጣኝ ምላሽ ስጡን። ከኛ በኋላ በዚህ ችሎትበሽብር የተከሰሱ ሁሉ ተፈተዋል።እኛ ቀጠሮ ብቻ ነው እየተሰጠን ያለው። የጋምቤላ ተወላጅ በመሆናችን ከሌሎች ተለይተን ለምን እኛ እንቀራለን? ማረሚያ ቤትም ለሌሎች ምህረቱ ለሚመለከታቸው የሚሞላ ፎርም ሲሰጥ ለኛ አልተሰጠንም። የኛ ቤተሰብ በየቀጠሮ እየተመላለሱ እየተንከራተቱ ነው። እዚህ ችሎት ለመከታተል ከተቀመጠው ግማሹ ከጋምቤላ የመጣ ነው። የክልላችን መንግስት ከአንድም ሁለቴ እንድንፈታ ለአቃቤ ህግ ቢልክም ምላሽ አልተሰጠንም። “
👉ዛሬ በ4ኛ ችሎት ቀጠሮ የነበራቸው በሽብር የተከሰሱት እነ ገብሬ ንጉሴ፣ ደስታ መንገሻ፣ ኦጁሉ ኦፒዎ እና ደረጄ አለሙም በተመሳሳይ ለሰኞ ከሰአት ተቀጥረዋል።