እኛ የአባቶቻችን ልጆችና የዚህች ጎስቌላ ኢትዮጵያ ተረካቢዎች ይህንን በርግጠኝነት እንናገራለን።
እኛ በምንገነባት ኢትዮጵያ፤
• የእኛ ልጆች እንደ እኛ ቡትቶ ለብሰው አያድጉም።
• የእኛ ልጆች ህልማቸው ጠግቦ ማደር
ሳይሆን ከምንሞላው የኢትዮጵያ ጎተራ ለተራቡት መለገስ ይሆናል።
• የእኛ ልጆች ትግላቸው ከድህነት ማጥ ለመውጣትሳይሆን የበለፀገች ኢትዮጵያን ዓለም ማማ ላይማውጣት ነው።
• የእኛ ልጆች እርስ በርስ መፈላለጊያቸውናመፈቃቀሪያቸው ዘራቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊነታቸውይሆናል።
• አባቶቻችን ከአባቶቻቸው ተረክበዋትና አጎሳቁለዋት ያስረከቡንን ኢትዮጵያ እኛ ጎስቌላ ልጆቻቸው ግን፤ የበለፀገችና ልጆቿን ያበለፀገች፤ የተከበረችና ልጆቿን ያከበረች፤ የታፈረችና ሰው መሆንን ያስቀደመች፤ ህግማውጣት ብቻ ሳይሆን ለህግ የተገዛች፤ የታመነችና በዜጎቿ የምትተማመን፤ ሀገራዊ ዝርፊያንና ሀገራዊ ሌብነትን የተጠየፈች፤ አፈናንና ጭቆናን ሰብዓዊመብት ገፈፋንና ኢሰብዓዊ ሰቆቃን ከምድሯ ያስወገደች፤ ቂም በቀልንና ዘረኝነትን ያንበረከከች፤ ሠላም ፍቅርና አንድነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናስረክባለን!!
እናንት የዚህ ጎስቌላ ትውልድ ጋዜጠኞች ሂዱና በምድሪቱ ሁሉ ለኛ ትውልድ ይህንን ንገሩ!!!
ታህሳስ 2011 ዓ/ም (ጃንዋሪ 2019)
ሲድኒ አውስትራሊያ
mmtessema@gmail.com