ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በበሽታው ተይዘው የሞቱ ሰዎች ቁጥር አራት መድረሱ ታወቀ። በኮቪድ 19 ሕይወታቸውን ያጡ አራተኛዋ ሰው የ75 ዓመት ሴት መሆናቸውንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ይፋ አድርገዋል::
እኚህ ኢትዮጵያዊት ሴት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ከመሆኑ ባሻገር በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በመጣራት ላይ መሆኑን የጠቆመው መግለጫ፣ ግለሰቧ በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ ውጤት ውስጥ የተካተቱ ናቸው።
ታማሚዋ በተጓዳኝ ሕመም ሆስፒታል ተኝተው ሲታከሙ ቢቆዮም ባጋጠማቸው የመተንፈስ ችግር በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ናሙና ከተወሰደ በኋላ፣ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ሕይወታቸው ማለፉንም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አራት ደርሷል። መድረሱንም ዶክተር ሊያ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል።

























