ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡–መንግሥት ለዘርፉ የብድር አገልግሎት ማመቻቸት ባለመቻሉ፣ እንዲሁም ለውጭ ኢንቨስተሮች ብቻ ትኩረት በመስጠቱ ምክንያት ለችግር ተዳርገናል ብለዋል የማኅበሩ አባላት።
በተጨማሪም በኮቪድ 19 ምክንያት የተከሰተውን ችግር ተቋቋሞ መቀጠል እንደከበዳቸውና ከአንድ ወር በኋላ ለሠራተኞቻቸው መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።
ከዘርፉ እንድንወጣ እየተደረግን ነው የሚሉት ባለሙያዎች ለአገር ውስጥ ባለ ሀብቶች በሴክተሩ ከቆዳ ማስረከብ ጀምሮ ያለውን ሒደቶች ለማከናወን ከወረርሽኙ ጎን ለጎን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር እንዳለባቸው የቆዳ ፋብሪካዎች ማኅበር አባላት ተናግረዋል።

























