የዓለም ጤና ድርጅት የጭንብል አጠቃቀምን በተመለከተ አዲስ መመሪያ አወጣ

የዓለም ጤና ድርጅት የጭንብል አጠቃቀምን በተመለከተ አዲስ መመሪያ አወጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ድርጅቱ ቀደም ሲል ስለአፍናጫና አፍ ጭንብል መሸፈኛ አጠቃቀም አውጥቶት የነበረውን መመሪያ ለውጫለሁ ብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ከዚህ በፊት ያወጣውን የጭንብል አጠቃቀም መመሪያ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የተገደደው፤ በሽታው ያለባቸው ሰዎች ምልክት ከማሳየታቸው በፊት በሽታውን ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ማስረጃዎች መገኘታቸውን ተከትሎ መሆኑን ገልጿል።
የጤና ተቋሙ ባወጣው አዲስ መመሪያ ” አሁንም የሕክምና ጭምብል ሁሉም ሰው መጠቀም የለበትም” ብሎ፤ ነገር ግን ከተለያዩ ጨርቆች የሚዘጋጁ እና አስፈላጊ ከሆነም ቤት ውስጥ ማዘጋጀት የሚቻሉትን ጭንብሎች መጠቀም ይቻላል ሲል ጥቆማ አድርጓል።
የሕዝብ ትራንስፖርት ላይ፤ የገበያ ቦታዎች በመሳሰሉትና አካላዊ ርቀትን በአግባቡ ለመጠበቅ በማይቻልባቸው ስፍራዎች ላይ፤ ሁሉም ሰው ከጨርቅ የተሠሩ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ማድረግ እንደሚገባ ግን ዓለም ዐቀፉ የጤና ተቋም ምክር ለግሷል።
በቀጥታ ከኮሮናቫይረስ ጋር ግንኙነት የሌላቸው የተለያዩ ክፍሎች ላይ የሚገኙ የጤና ሠራተኞች ጭምር ለሕክምና ባለሙያዎች የተዘጋጁ ጭንብሎችን ማድረግ ግድ ነው ያለው ድርጅቱ፤ ቀደም ሲል የሕክምና ጭምብል መጠቀም ያለባቸው የጤና ሠራተኞች፣ የኮሮናቫይረስ ሕሙማን እና የሕሙማኑ እንክብካቤ የሚያደርጉ ሰዎች ብቻ ሊሆኑ እንደሚገባ መናገሩ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY