ለአዲስ አበባ ወጣቶች 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በብድር ተበጅቷል ተባለ

ለአዲስ አበባ ወጣቶች 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በብድር ተበጅቷል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በቀጣዮ ከ280 ሺኅ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እሠራለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።

የታከለ ኡማ አስተዳደር ለሥራ እድል ፈጠራ በብድር መልክ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡንም እወቁልኝ ብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት በሥራ እድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ባካሄደበት ወቅት ነው ከላይ የተገለጸው ሀሳብ የተንጸባረቀው።
ሴቶችን እና ወጣቶችን በተለያዩ የሥራ ዘርፎች በማሠማራት ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ያመላከተው መረጃ፤
በተጀመረው በጀት ዓመትም የብድር እና የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ችግሮችን በመፍታት ለ280 ሺኅ ያህል ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን ያስረዳል።
ሀሳቡን ከግብ ለማድረስ ከመንግሥት እና ከግሉ ዘርፍ ጋር በቅንጀት ለመሥራት ታሳቢ የተደረገ ከመሆኑ ባሻገር፤ የሥራ እድሉ እድገት ተኮር በሆኑት በከተማ ግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፎች ሰፊ ትኩረት ያደርጋል ነው የተባለው።
ለፕሮግራሙ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም በብድር መልክ የከተማ አስተዳደሩ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በጀት መድቤያለሁ ብሏል።

LEAVE A REPLY