“ከመንግስት ካዝና የተዘረፈን ጨምሮ” ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ!

“ከመንግስት ካዝና የተዘረፈን ጨምሮ” ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የመገበያያ ገንዘቦችን የያዙ ግለሰቦች በተደረገ የፖሊስ ፍተሻ በጎንደር አንዳቤት ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአንዳቤት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል።

ግለሠቦቹ ከጎንደር ጭነው ሲመጡ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አንዳቤት ከተማ ላይ በተደረገ ፍተሻ 1 ሺህ 500 በላይ ጥይቶች፣ 3 ክላሽንኮቭ፣ 1 ካዝና እና 37 ሺህ 700 ብር በቁጥጥር ስር እንደዋለና መሳሪያውን ሲያዘዋውሩ የነበሩት 3 ግለሰቦችና የመኪና አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል።

ግለሰቦቹ የሃሰት መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል ያሉት የአንዳቤት ወረዳ የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሲሳይ እንየው “ግለሰቦቹ የያዙት ህገ ወጥ ጥይት ከመንግስት ካዝና ጭምር የወጡ እንደሆነ መረጃው ያመላክታል። ግለሰቦቹም ህጋዊ ነን በማለት ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል” ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY