የእናት ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ታሰሩ!

የእናት ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ታሰሩ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ጋሞ ዞን፣ ከምባ ወረዳ ምርጫ ክልል የእናት ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት መምህር በድሉ አለባቸውን አስሯል።  “ግርግር አስነስተዋል” በሚል ምክንያት ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት መታሰራቸውን ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

“ጉዳዩ በቀላሉ ይፈታል የሚል ግምት የነበረን ቢሆንም ቃላቸውን ተቀብለን እንላቀቸዋለን በሚል ሽንገላ የከምባ ከተማ ፖሊስ እስካሁን ድረስ አስሮ ይዟቸዋል” ያለው ፓርቲው “በዚህ ጊዜ የሚደረግ እንዲህ ያለ መሠረተ ቢስ ክስ የእጩዎቻችንን መልካም ስምና ዝና ሆን ተብሎ ለማጉደፍና ለሌሎች እጩዎችም የማስፈራሪያ መልዕክት ለማስተላለፍ ያሰበ እንጂ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዳልሆነ እንረዳለን” ሲል ገልጿል።

እናት ፓርቲ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ በገለፀበት በዚሁ መግለጫው “እስሩ ፖለቲካዊ እንድምታ ያለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈቱ” ሲል አሳስቧል።

LEAVE A REPLY