ሩሲያ እና ዩክሬን ቀውስ ከሚያባብስ ድርጊት እንዲቆጠቡ ጠ/ሚ አብይ አሰሰቡ

ሩሲያ እና ዩክሬን ቀውስ ከሚያባብስ ድርጊት እንዲቆጠቡ ጠ/ሚ አብይ አሰሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሁሉም ወገን ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅቦ ግጭቱን ለመፍታት ሁልንተናዊ የሰላም መንገዶችን ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ።

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዩክሬን ቀውስ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዩክሬን ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በቅርቡ ካለፈችበት ጦርነት ተነስታ ስለ ጦርነት ጉዳት የምታካፍለው ሰፊ ልምድ አላት ብለዋል። የኢትዮጵያ ልምድ ጦርነት ቤተሰብን፣ ማህበረሰብ ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚን ክፉኛ የሚጎዳ፣ አጥፊ ነው ” ሲሉ ገልፀዋል። ጦርነት የሚያደርሰውን ቁሳዊ ጉዳት መጠገን ቢቻልም በማህበረሰብ ላይ ጥሎት የሚያልፈውን ጠባሳ ግን ለማከም ከባድ መሆኑን አመልክተዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የዩክሬን ወቅታዊ ቀውስ በቅርበት እየተከታተለች ነው ” ያሉ ሲሆን ግጭቱን የሚያባብሱ ሁኔታዎች እንደሚያሳስባት ገልፀዋል።

ሁሉም ወገኖች ቀውስን ከሚያባብስ ድርጊት ታቅበው ግጭቱን ለመፍታት ሁልንተናዊ የሰላም መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል። በአካባቢው ላይ ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ምኞት ግለፀዋል።

LEAVE A REPLY