በድርቅ መክንያት በቦረና፣ በምስራቅ ባሌና በሶማሌ ክልል 377 ትምህርት ቤቶች  ተዘጉ

በድርቅ መክንያት በቦረና፣ በምስራቅ ባሌና በሶማሌ ክልል 377 ትምህርት ቤቶች  ተዘጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ብቻ 61እንዲሁም በሶማሌ ክልል ደግሞ 316 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸው ተነገረ።

በሁለቱ ክልሎች በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ለፍተኛ ጉዳት ተጋልጠዋል።

በኦሮሚያ በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፣ ምስራቅ ባሌ ዝቅተኛ ቦታዎች፣ በቦረና፣ በምእራብ ጉጂ ዞኖች በርካቶች ለከፋ ችግር እና ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።

በክልሉ በአምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 40 ወረዳዎች 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን እንስሳት ተጠቅተዋል ፣ 257 ሺህ አቅም አንሷቸዋል ሲል የብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለዶይቼ ቬለ ተናግራል።

የኮኒሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደበበ ዘውዴ እንዳሉት በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፣ በቦረና ፣ በምዕራብ ጉጂ ፣ በምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በሚገኙ 70 ወረዳዎች ውስጥ በ605 ቀበሌዎች 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ የመጠጥ ውኃ ይፈልጋል።
ድርቁ በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ባሉ 14 ወረዳዎች ብቻ 61 ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጉንም ገልፀዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ከ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ የተባለ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 8 ሺህ 244ቱ በአዲሱ ድርቅ ተጠቂ የሆኑ ናቸው ሲሉ ደበበ ዘውዴ ተናግረዋል።
ለሁለቱ ዞኖች 254 ሺህ ኩንታል እህል ለ853 ዜጎች መላኩንም በመግለፅ፤ ለተቀሩት የድርቅ ተጠቂ አካባቢዎች ደግሞ በመደበኛው የሥርጭት መርሃ ግብር እንዲደርሳቸው እየተደረገ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል በ83 ወረዳዎች 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሕዝብ ለውኃ እጥረት መጋለጡ ተሰምቷል። በዚሁ ክልል ከሀምሌ እስከ የካቲት ባለው የድርቅ ጊዜ 864 ሺህ 43 እንስሳት መሞታቸውን ኃላፊው ለራዲዎ ጣቢያው ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY