10 ድምጻዊያን ገቢውን ለኮሮና መከላከል ያደረጉት አልበም ሊወጣ ነው

10 ድምጻዊያን ገቢውን ለኮሮና መከላከል ያደረጉት አልበም ሊወጣ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና-ገቢው ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መከላከያ የሚውለው  “ንጋት” የተሰኘ አዲስ አልበም በቀጣዮ ሳምንት መጀመሪያ በገበያ ላይ ይውላል ተባለ። 

በአልበሙ ውስጥ የተካተቱት ዘፈኖች በሙሉ በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙሪያ ያተኮሩ ናቸው ተብሏል።
“ንጋት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ አልበም  በኢትዮጵያ የሙዚቀኞች ማኅበር ሕብረት የተዘጋጀ መሆኑም ታውቋል።
ከወጣት አቀንቃኞች ቆየት ያሉ አንጋፋ ድምጻዊያን ባቀነቀኑበት አልበም ላይ ፤ ዘሪቱ ከበደ፣ ዘሩባቤል ሞላ፣ ቤቲ ጂ፣ ቸሊና፣ ሀይሌ ሩት፣ ጆኒ ራጋ፣ ፍቅር አዲስ ነቃጥበብ ፣ ጌቴ አንለይ  እና ራሔል ጌቱ (ጥሎብኝ)   ተሳትፈውበታል።
አልበሙ የኮሮናቫይረስ ላይ በማተኮር የተዘጋጀ ሲሆን ገቢውም ለዚሁ ቫይረስ መከላከያ እንዲውል በማሰብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስጦታ መበርከቱም ለማረጋገጥ ተችሏል።
 ንጋት የሙዚቃ አልበምን በአሞሌ የስልክ መተግበሪያ ላይ ከሰኞ ጀምሮ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ማግኘት ይችላል።

LEAVE A REPLY