ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጸብ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ጠ/ሚ/ር አብደላ ሀምዶክ ገለፁ

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጸብ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ጠ/ሚ/ር አብደላ ሀምዶክ ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሱዳን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጸብ የመፍጠር ዓላማ እንደሌላት ነው ያብራሩት።

“እየተናፈሰ እንዳለው ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ የተለየ የድንበር ችግር ጉዳይ የለም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፤ ይህ ቀደም ሲልም በተለያዩ ጊዜያት የነበረ  መሆኑን ጠቁመው ፤ ሱዳን ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት ጋር የድንበር ችግሮች ሲያጋጥሟት እንደቆየም አስታውሰዋል።
“ከኢትዮጵያ ጋር ያለን ግንኙነት በባህል ፣ በታሪክ እና በመልክዐ ምድር እና በመልካም ጉርብትና የተሳሰረ ነው። በመካከላችን የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶችም አሉን” ሲሉ የተደመጡት የሱዳኑ መሪ፤ ሰምኑን የተፈጠረውን ክስተትም በዚህ መንገድ ይፈታል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።

LEAVE A REPLY