የሰጡህን ብቻ ተቀበል የፖለቲካን ባሕል የለውጡ ቡድን ሊቀይረው እንደሚገባ ፕ/ር አሕመድ ዘካሪያ...

የሰጡህን ብቻ ተቀበል የፖለቲካን ባሕል የለውጡ ቡድን ሊቀይረው እንደሚገባ ፕ/ር አሕመድ ዘካሪያ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮች ፖለቲካችንን የጋራ ማድረግ ስላቃተን የተፈጠሩ ናቸው ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያ ገለጹ።

ዛሬ ላይ ለዚህ ችግራችን መፍትኄ ልናበጅለት ይገባል ያሉት
ረዳት ፕሮፌሰሩ ፤ በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶች፤ ኹከቶችና መፈናቀሎች ከትላንት የወረስናቸው እና ፖለቲካችንን የጋራ ማድረግ ስላቃተን የተፈጠሩ ናቸው ብለዋል።
“ፖለቲካችን ሁልጊዜ ይዞ የሚሮጠው የጥቂቶችን ፍላጎት ተንተርሶ ነው” ሲሉ የተደመጡት ረዳት ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ፤ የመነጋገር፤ የመወያየት፤ የመግባባት ባህል የሌለን መሆኑ ደግሞ ችግሩን አስፍቶታል ሲሉም ገልጸዋል።
ያለን የሰጡህን ብቻ ተቀበል የሚል ፖለቲካዊ ባህል እንደሆነ የጠቆሙት ፕሮፌሰሩ፤ ይህንን ባህል አሁን ያለው የለውጥ መንግሥት ሊቀይረው ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
ብዙኃን የሚስማሙበት፤ የፖለቲካ ልሂቃን የመከሩበትና ከኢትዮጵያውያን ማንነት ጋር አብሮ የሚሄድ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሊኖረን እንደሚገባ የገለጹት ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያ፤ ይህ ሲሆን ብቻ ለዘመናት ሲከተለን የቆየው የፖለቲካ ቁርሾ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትኄ ያገኛል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY