አብንና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በማይካድራ ከተማ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ

አብንና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በማይካድራ ከተማ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህወሓት ኃይል በአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ተመትቶ ለመሸሽ በተገደደበት ወቅት በማይካድራ ከተማ ነዋሪ በሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አብንና የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አወገዙ።

በማይካድራ ነዋሪዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን የአማራ ብዙኃን የዘገበ ሲሆን፤ በማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረገ መሆኑን የጠቆመው ቢቢሲ ደግሞ ለጊዜው እንዳልተሳካለት ገልጿል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ በሽሽት ላይ ያለው ታጣቂ ኃይል በማይካድራ ከተማና አካባቢው የነበረው የትሕነግ ጦር፣ ከተማዋን ከመልቀቁ በፊት ንፁሀን ሰላማዊ ዜጎችን በአማራ ማንነታቸው ብቻ ለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደፈፀመባቸው ተረጋግጧል ከማለቱ ባሻገር፤ በጥቃቱ ሕጻናትና ሴቶች ሳይቀሩ በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ መገደላቸውንም ይፋ አድርጓል።
 ጥቃቱ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ያለው የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ፤ ” ድርጊቱ በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ የታሰበ ነው፤ የአማራ ሕዝብ ፣ የትግራይን ሕዝብ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ከየትኛውም ጥቃት ጥላ ከለላ ሁነህ ይህን ጊዜ እንድታሳልፈው ይሁን” ሲል መልእክት አስተላልፏል።
በቀጣይም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ የሚል ስጋት ያለው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፤ መንግሥት የቅድመ መከላከልና ንፁሃንን የመታደግ ሥራ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስቧል።

LEAVE A REPLY