125 ከተሞች በስድስት ወር የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸው ተሰማ

125 ከተሞች በስድስት ወር የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ባልተዳረሰባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ፍትሀዊ ተደራሽነት እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሥራዎች እያከናወንኩ ነው አለ።

ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት 161 አዳዲስ ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያኙ ለማድረግ አቅዶ፣125ቱ  የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጿል።
በመልሶ ግንባታ ሥራ ደግሞ  10 ከተሞችን ማገናኘት ተችሏልም ያለው ተቋሙ፤ በአዲስና በመልሶ ግንባታ ሥራዎች 171 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ አቅዶ 135ቱን ማሳካቱም ተሰምቷል።
በተጨማሪ ባለፉት ስድስት ወራት የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 1 ሺህ 35 ነጥብ 15 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ቢወጠንም፤ 1 ሺህ 439 ነጥብ 67 ኪሎ ሜትር  በመዝርጋት ከዕቅድ በላይ ለማሳካት መቻሉን ባለሥልጣን መ/ቤቱ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY