ሜ/ጀነራል ገብረመድህንን (ወዲ ነጮ) ጨምሮ 12 የጁንታው አባላት ላይ ክስ ሊመሠረት ነው

ሜ/ጀነራል ገብረመድህንን (ወዲ ነጮ) ጨምሮ 12 የጁንታው አባላት ላይ ክስ ሊመሠረት ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የጁንታውን የጥፋት ዓላማ ለማስፈጸም ሆን ብለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሬዲዮ ግንኙነትን በማቋረጥ ሰሜን ዕዝ ጦር ላይ ጥቃት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉት የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ እነ ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲነጮ) ክስ በ15 ቀን ውስጥ ክስ ሊመሠረትባቸው ነው።

በዛሬው ዕለት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡
ክስ መመስረቻ የተጠየቀባቸው ተጠርጣሪዎች ፦
– የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ሜ/ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ፣
– ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረመድህን፣
– ብርጋዴር ጄኔራል አብርሃም መውጫ፣
– ኮሎኔል ገብረህይወት ደስታ፣
– ኮሎኔል ዮሃንስ በቀለ፣
– ኮሎኔል ዘመን ታመነ ፣
– ሻለቃ ገብረእግዚአብሄር ግርማይ፣
– ሌተናል ኮሎኔል ተክለ ኃይሉ፣
– ሌተናል ኮሎኔል ምሩጽ ወልደአረጋይ፣
– ሻለቃ ኃይለስላሴ ግርማይ እና ሻለቃ ብርኃኔ ገብሩ መሆናቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY