አሜሪካ ዜጎቿን በድጋሚ አስጠነቀቀች!

አሜሪካ ዜጎቿን በድጋሚ አስጠነቀቀች!

  • በኢትዮጵያ የድንበር ከተሞች ዜጎቿ እንዳይደርሱ አሳስባለች!

/Ethiopia Nege/ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ወር በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ዜጎቹ ያወጣውን የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማራዘሙን በድጋሚ ይፋ አደረገ።

ስቴት ዲፓርትመንት ከኖቨንበር 2015 ጀምሮ በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ በመጥቀስ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማራዘም በተጠናከረ መልኩ ባተተው መግለጫው በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ መስራት አስቸጋሪ መሆኑን ገልጾ ከዜጎች ጋር በድንገት የስልክ ግንኙነት መቋረጥ ሊከሰት እንደሚችል አስታውቋል።

በመግልጫው በድንገትና ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሚከሰት የኢንተርኔትና የስልክ መቋረጥ በመላ ሀገሪቱ በተደጋጋሚ እንደሚከሰት አብራርቶ አሜሪካን ዜጎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት አስቸጋሪ እንዳደረገበት አትቷል።

አሜሪካዊያን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች በሚገኙ ከተሞች ሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከ10 እስከ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት እንዲሆን ያስጠነቀቀው የአሜሪካ መንግስት መግለጫ ከማናቸውም የሰላማዊ ሰልፎችና በርከት ያሉ ሰዎች የተሰበሰቡበት አካባቢ እንዳይገኙና ራሳቸውን እንዲጠብቁ አስጠንቅቋል።

ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የሚያደርጉ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የስልክ ቁጠራቸውንም ለኢምባሲው እንዲያስመዘግቡ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤቱ አሳስቧል።

/Ethiopia Nege December 8, 2016/

LEAVE A REPLY