የብሪታንያ መንግስት አቶ አንዳርቸው ፅጌ ከእስር እንዲለቀቁ ግፊት እንዲያደርግ ተጠየቀ

የብሪታንያ መንግስት አቶ አንዳርቸው ፅጌ ከእስር እንዲለቀቁ ግፊት እንዲያደርግ ተጠየቀ

/Ethiopia Nege News/:- ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  ማክሰኞ ዕለት ወደ ለንደን ያመሩት  “በለንደን  የሶማሊያ ጉባኤ”  ላይ ለመሳተፍ ሲሆን በቆይታቸውም ከጠ/ሚንስትር ተሬሳ ሜይና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጋር ይገናኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፕሪቭ  የተባለ የብሪታንያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ዛሬ ባወጣው  መግለጫ  ገልጿል።

ከየመን ታፍነው ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱት አቶ አዳርጋቸው  ፅጌ በመጭው ሰኔ ወር ሶስት አመት የሚሞላቸው ሲሆን የብሪታንያ መንግስት ከእስር ተለቀው ወደ  ለንደን እንዲመለሱ ጫና እንዲያደርግ  በቤተሰቦቹና በብሪታንያ ፖርላማ አባላት  ግፊት ሲደረግ ቢቆይም  የተጀመረ ነገር ባለመኖሩ እንዳሳዘነው ሪፕሪቭ (Reprieve) አስረድቷል።

እኤአ በ2009  የአቶ ኃይለማርያም መንግስት፤ አቶ አንዳርጋቸውን በውሸት ፖለቲካዊ ክስ ከሶ የሞት ፍርድ ባስተላለፈበት ጊዜ፤ አንዲ ከቤተሰቡ ጋር በለንደን በሰላም ይኖር እንደነበረ ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

የሪፕሪቭ ም/ኃላፊ የሆኑት ሀሪት ማክ፤ የብሪታንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን  በአሳፋሪ ሁኔታ ታፍነው በሞት ቀጠና ውስጥ አዲስ አበባ የሚገኙትን  ብሪታናንያ ዜጋ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን  ለማስለቀቅ አሁን በለንደን ከሚገኙት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር  ቅድሚያ ሰቶ እንዲመክሩ በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

  /Ethiopia Nege May 11, 2017/

LEAVE A REPLY