ቴዲ አፍሮን ቃለ- መጠይቅ ያደረገው ጋዜጠኛ ኢቢሲን ለቀቀ

ቴዲ አፍሮን ቃለ- መጠይቅ ያደረገው ጋዜጠኛ ኢቢሲን ለቀቀ

/Ethiopia Nege News/:- ከአራት ዓመት በላይ ከኢቢሲ(EBC) ጋር ያሳለፈው ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ ባለፈው ሳምንት አርቲስ ቴዲ አፍሮን በመኖሪያ ቤቱ “ ለእሁድ መዝናኛ” የሚሆን ፕሮግራም ሰርቶ ሀሙስ ግንቦት 12/2017 ከሙሉ ፕሮግራሙ ላይ ተቀንጭቦ በኢቢሲ ና በእራሱ በጋዜጠኛው ፌስቡክ ገፅ ላይ ለቅምሻ የሚሆን ከተለቀቀ ከሰአታት በኋላ ኢቢሲ ከፌስቡክ ገፁ ላይ አንስቶ ለጣቢያው ቅርብ በሆነ ግለሰብ ፌስቡክ ገፅ

‘ እርማት” በማለት የቴዲ አፍሮ ቃለ ምልልስ እሁድ እንደማይቀርብ ተገለፀ።

የፕሮግራሙ መሰረዝ ምክንያት አሁንም ድረስ በግልፅ የተባለ ነገር ባይኖርም የስርዓቱ ካድሬዎች ግን ለሁለት ተከፍለው በዚሁ ማህበራዊ ድህረ-ገፅ ላይ ሲወዛገቡ ታይተዋል።

አንዱ ቡድን ቴዲ አፍሮ “ፀረ ብዝሃነት” ነው ብለው ሲከሱ ሌው ደግሞ ተቋሙ የተለያዩ ሀሳቦች የሚሸራሸሩበት እንዲሆን መፍቀድ አለብን ሲሉ ተስተውለዋል።የኦሮሚያ መንግስት ኮምኒኬሽን ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ ከአርቲስቱ ጋር የተሰራው ፕሮግራም አየር ላይ እንዲውል በገደምዳሜው ሲሞግቱ ታይተዋል።

በብዙዎች እምነት ለፕሮግራሙ መሰረዝ ዋና ምክንያት መንግስት በእጅጉ አርቆ ያስቀመጠውን “ኢትዮጵዪዊነት” አርቲስቱ ደጋግሞ በመዘመሩ መሆኑን አይጠራጠሩም።

“ ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ አይደለም” የሚለው ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ “ ጉዳዩ አንድን የኪነ ጥበብ ሰው ማቅረብና ያለማቅረብ ጉዳይ ብቻ አይደለም።ጉዳዩ የጋዜጠኝነት ልዕልናም የሚጋፋ ሆኖ ስላገኘሁትና ብዙዎች መስዕዋት የከፈሉለትን ሙያ ክብር ለመስጠትም ጭምር ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስኩት።” በማለት ዛሬ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ለጥፋል።

“ይህን ውሳኔ ስወስንም የጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ላላችሁ፤ ጋዘጠኝነት በመማርና በማስተማር ላይ ላላችሁና መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ እያሰብኩ ነው። ለኢቢሲ አጠቃላይ ሰራተኞችና በተለያዩ መንገዶች ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ። ዝርዝር ሒደቱንም እመለስበታለሁ::” በማለት መልዕክት አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን/ብሮድካቲግ ኮርፖሬሽን (EBC) በሚያዚያ ወር መጨረሻ ላይ ለህ/ተ/ም/ቤት ባቀረው ሪፖርት “ ዘረኝነት፣ሙስንናና ከውስጥም ከውጭም ባሉ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የስራየ መሰረታዊ ችግሮች ናቸው “ በማለት ማስረዳቱ የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY