የ”ሜቴክ” ትሩፋቶች /ግዛቸው አበጋዝ-ሳስካችዋን (ካናዳ)/

የ”ሜቴክ” ትሩፋቶች /ግዛቸው አበጋዝ-ሳስካችዋን (ካናዳ)/

በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን አንባገነን ስርአት በኢኮኖሚ እንዳይዳከም የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያገለግለውን “ሜቴክ” ወይንም ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ስንቶቻችን ነን በጠለቀ መልኩ የምናውቀው?

ዛሬ ላይ የያዘውን ስሙን ይዞ የኢትዮጵያን የሚካሄዱትን ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጠቅልሎ በመያዝ የህዝብን ሃብት ያለተቀናቃኝ መዝረፍ ብቻ ሳይሆን በርካታ የሲቪክ ተቋማትን በመጠምዘዝ “ሜቴክ” ስር አስገብቶ ለህውሃት ከፍትኛ ወታደራዊ መኮንኖች የምዝበራ አኬልዳማ እንዳሚያደርጋቸውስ?

“ሜቴክ” በ2010 በሚንስትሮች ምክር ቤት “ሜቴክ” ተብሎ ከመቋቋሙ በፊት በሀገር መከላከያ ሚኒስትር የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ በስሩም በብ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው የበላይ አመራርነት የመከላከያ ኢንዱስትሪዎችን ያስተዳድር ነበር፡፡ ተቋሙ በመከላከያ ስር መሆኑ ብዙዎቹ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባል ናቸው፡፡ በተጨማሪም ሲቪል ሰራተኞችን በስሩ ይቀጥራል፡፡

ነገር ግን የዚህ ተቋም ከበላይ ስራ አስኪያጅ ጀምሮ ብዙውን አስተዳደሩን የያዙት እስከ በር ጥበቃ ድረስ የአንድ ብሄር ወይንም የትግራይ ተወላጆች ሆነው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በወታደር ቤት አደረጃጀት የበታች ሹም ለበላዩ ሹም የሚገባውን ክብር መስጠት ግዴታው ሲሆን፤ በዚህ ተቋም ውስጥ የሚታየው ከወታደራዊ ትምህርት የተለየ ነው፡፡ በዚህ የጥቂቶች የበላይነትን ባሰፈነው ህውሃት መራሹ ስርአትና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ከትግራይ ልጆች ውጪ የሌላውን ብሄር መናቅ፣ መግፋት የተንሰራፋ ነው፡፡ በማንነትሀ ብቻ ተዋርደህ ትኖራለህ፡፡ በብቃት ሳይሆን በማንነት ትመዘናለህ፡፡ የመብትና የአስተዳደር ጥያቄ ካነሳህ ታፔላ ለጥፈው፣ አሸማቀውህ አንገትህን ያሰብሩሃል፡፡ በተቃራኒውም ለአሸማቃቂዎችህ እና ለራሳቸው ብሄር ልጆች ያልተገደበ መብት እና ጥቅማ ጥቅም ይሰጡዋቸዋል፡፡

ዘርፉ ትልቅ እውቀት የሚያስፍልገው ቢሆንም ለእውቀትና ለሞራል ዴንታ የሌላቸው ከፍተኛ የህውሃት መኮንኖች ዘርፉን በማን አለብኝነት ተቆጣጥረውት እውቀቱና አቅም ኖሩዋቸው ስንት ሊሰሩ የሚችሉ ወታደር የምህንድስና ባለሞያዎችን እንደእባብ ራስ ራሳቸውን እየቀጠቀጡ የስነልቦና ቀውስ ውስጥ ከተዋቸዋል፡፡ ስንቱን ከሀገር አሰኮብልለዋል፡፡ ስንቱን ባለሙያ እስር ቤት አጉረዋል፡፡

ስርአቱን የማይደግፍ በተቋሙ ውስጥ ከተገኘ የሀገር ጠላት በማስመሰል እና በተለመደው ፍረጃቸው የድሮ ስርአት ናፋቂ፣ ነፍጠኛ እና ልማት አደናቃፊ የሚል ቅጽል ስም አውጥተው ይለጥፉልሃል፡፡ አንተን አንገት አስደፍተው አንድትኖር ሲያደርጉህ እምቢ አንገቴን አልደፋም ብለህ አሻፈረኝ የምትል ከሆነ ደግሞ እንደእኔና እንደበርካታ የድርጅቱ አባላቶች በወታደራዊ እስር ቤቶች ይከረቸምብሀል፡፡ በጠባብ ኮንቴይነር ውስጥ ታጉረህ ይህ ነው የማይባል በደል ትቀበላለህ፡፡ በብ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው ዘመን መብታችንን በመጠየቃችን የደረሰብን መገለል፣ መዋከብ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፣ እስር እና መከራ መቼም ቢሆን ከአይምሮ አይጠፋም፡፡ (የዚህ ፅሁፍ ፀሀፊ ለበርካታ አመታት በሚቴክ ያገለገለና አሁን ስርአቱን ከድቶ በስደት ካናዳ የሚኖር ነው፡፡)

የህውሀት የመከላከያ መኮንኖች እንደ ዛሬ ዘርፈ ብዙ የሆነ የዘረፋ ተቋማትን ማለትም እነ ”ሜቴክ” ከማቋቋማቸው በፊት ሀገሪቱዋን በተለያየ መልኩ ሲዘርፉ ቆይተዋል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ቤተስቢቻቸውንና ዘመዶቻቸውን እያሰባሰቡ እንዲሁም እራሳቸው በሚያደራጁት ቡድኖች በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን በውሸት ጨረታ አውጥቶ የተቋሙ ስራዎችን በመስጠት በህዝብ ሀብት በመቀለድ የዘመዶቻቸውን ኪስ ያደልባሉ፡፡ ተፈፃሚነት የሌላቸውን እቅዶች በማወጣት የስራ ማካሄጃ በሚል በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ይዘርፉበታል፡፡ ከአንድ ከሁለት ስብሰባ በኋላ እቅዱ ስሙም እንቅስቃሴውም የውሀ ሽታ ይሆናል፡፡

በ2010 የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚለው ስም ተቀይሮ “ሜቴክ” ወይም ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሲባል ልክ እንደቀድሞው በመከላከያ ሚኒሰትር ስር ሆኖ የህውሃት መኮንኖች ኮርፖሬሽኑን በስፋት መልሰው ተቆጣጥረውታል፡፡ ከበፊቱ የሚለየው በፊት ከነበሩት የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ የሲቪል ኢንዱስትሪ ተቋማቶችን ጠቅልሎ መያዙ ነው፡፡ በሀገሪቱዋ ያሉትን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ያለምንም ተፎካካሪ ከመንግስት እየተሰጠው ፐሮጅክቱን ከማስፈጸም ይልቅ የፕሮጀክቶቹን ገንዘብ በመመዝበር እስከዛሬ ድረስ አለ ለምሳሌ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ፡ ስኳዋር ፋብሪካ ፡አባይ ግድብ እና የመሳሰሉት፡፡ ሌላው የ ”ሜቴክ” ቁልፍ ችግር ከትልልቅ ጀምሮ እስክ ጥቃቅን ያሉ የብረታ ብረት ስራዎችን ጠቅልሎ የመያዝ ፍላጎቱ ነው በዚህም የተነሳ ትንሽ የማይባሉ እንደ ብረታ ብረትና ማሽነሪ ያሉ የግል ተቁዋማትን ከዘርፉ አስወጥቶዋቸዋል፡ በተቃራኒው ግን የራሱ የሆኑ የትግራይ ብሄር ተወላጆችን በቡድን በቡድን አደራጅቶ መነሻ ካፒታል እየሰጠ የ ”ሜቴክ”ን አንስተኛ ፕሮጀክቶች በኮንትራት እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡

የ ”ሜቴክ” ወታደራዊ መኮንኖች ምዝበራ ታሪክ በዚህ ብቻ የሚገታ አይደለም ፡፡ የማውቀውን አንድ ሁለት ምሳልዎች ልጨምር ፡፡ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የድርጅቱ ዋና ፅህፈት ቤት ጨምሮ በቂ የሚባሉ ህንጻዊች ቢኖሩትም በየከተማው ውስጥ ያሉትን ትልልቅ ህንጻዎችና ሆቱሎችን ለቢሮና ለእግዳ ማረፊያ በሚል ስም በመከራየት በየወሩ በኪራይ ስም በብዙ መቶ ሺ ብሮችን ይመዘብራሉ፡፡ ሌላው ደግሞ በውጪ ሀገር የማሽነሪን ግዚዎችን ይመለከታል፡፡ይህ በጣም ከባዱ የላጥ ላጥ ዘረፋ መንገዳቸው ነው፡፡ ይህን ዘረፋ ከሌሎቹ ዘረፋዎች ለየት የሚያደርገው በዚህ ግዢ ውስጥ ለመሳተፍ በዋነኝነት የስርአቱ ታማኝ አግልጋይ መሆን ብቻ በቂ አይደለም ሚስጢር ጠባቂነትህ ይፈተሻል፡፡

በአገልጋይነት እና ሚስጢር ጠባቂነት ተፈትነህ ካለፍክ እውቀት እና ሙያ መሰረታዊ ጉዳይ አይደለም ለነሱ፡፡ ከዚያም የእጅ ጥፍራቸውን እናስበላ የሚያሰቆዝማቸው ምን አይነት ማሽን ቢገዛ የተቋሙን አቅም ያሳድጋል የሚለው ሳይሆን ሄጄ ምን ያህል ገንዘብ እሰራለው የሚለው ነው፡፡ ከዛም በኋላ አሮጌ ወይንም ብዙም ጥቅም የማይሰጡ ማሽነሪዎችን በጣም በርካሽ አንዳንዴም በነጻ ካስገቡ በኋላ አይናቸውን በጨው አጥበው አዳዲስና ዘመናዊ ማሽኖች ከፍተኛ ወጪ ወቶባቸው እንደተገዙ ለምስኪኑ ሰራተኛ ይገልጻሉ፡፡ ህብረተሰቡንም ራሳቸው በሚቆጣጠሩት ሚድያ በውሸት እግር ከወርች አስረው ለራሳቸው አዳዲስና ዘመናዊ ህንጻዎችን ይገነባሉ፡፡

በ ”ሜቴክ” ውስጥ የሚታዩ የአንድ ዘር የበላይነት፣ ምዝበራ፣ በደል፣ እስርና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዚች አጭር ጽሁፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ እውነት ታዲያ እነዚህ በዘር በድሎና እና በንዋይ የተለከፉ ዘረኞች ሀገሪቱዋን እና ህዝቡዋን ከረሃብ፤ከስቃይ፤ከእስርና ሞት በላይ ምን ለማረግ ነው አላማቸው የሚለው ጥያቄ ነው ውሰጤ የሚመላለሰው፡፡

ግንቦት 2009 ሳስካችዋን-ካናዳ

LEAVE A REPLY